mekdes-cfdc.com

Popularity: NO DATA

Mekdes-cfdc | mekdes child fostering development centre – የመቅደስ የህፃናት አዕምሮ ማበልፀጊያ ማዕከል የስራ-ዕቅድ ይህ የበጎ አድራጎት ማዕከል ግቡን እና አላማዎቹን ለማሳካት የተለያዩ ክንዉኖች መተግበር አስፈላጊ ነዉ ብሎ ያምናል፡፡ እነዚህ የስራ-ዕቅድ ክንዉኖች በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸዉ የላቀ የሀብት አሰባሰብ እና አጠቃቀምን ስርዓት መዘርጋት፤ የተለያዩ የሀብት አሰባሰብ ዕቅዶችን መተግበር እንዲሁም ማዕከሉን በብቁ የሰው ኃይል፣ በቁሳቁስ እና በቴክኖሎጂ የተደራጀ ማድረግ። ለታዳጊ ህፃናት ልጆች ተስማሚ የሆነ ለመኖሪያ ምቹ፣ ንፁህ እና ለአይን የሚማርክ የመኖሪያ ቤት እና አካባቢ መገንባት እንዲሁም አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ሟሟላት፡፡ ታዳጊ ህፃናትን የሚንከባከቡ አዋቂ ሰዎችን አስፈላጊ በሆኑ መመዘኛዎች በመጠቀም ምልመላ ማድረግና አስፈላጊዉን ቅድመ ስልጠና በመስጠት ዝግጁ በማድረግ ቅጥር መፈፀም፡፡ ለኑሮ ፈፅሞ በማይመች እና ለተለያዩ አደጋዎች ለተጋለጡ ወላጅ አልባ ታዳጊ ህፃናት ልጆችን ከተለያዩ የአገራችን ክልሎች የድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ ባስቀምጠው መመሪያ መሰረት ወደ ማዕከሉ መሰብሰብ፡፡ ለታዳጊ ህፃናት ልጆች ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን መስጠት

Category:
Visit Website