WordPress 6.2
2022
Popularity: NO DATA
Hidaya comparative – “ጂሃድ” የሚለዉ ቃል ሲወሳ ብዙ ሰዎች በተለይም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች አስፈሪ ምስል ይደቀንባቸዋል። ከተለያዩ የሚዲያ ምንጮች የሚያገኟቸው የተለያዩ መረጃዎች በዚህ አረዳዳቸው ላይ የራሳቸው ተፅእኖ አላቸው። እነዚህ ሰዎች ስለ ጂሃድ ሲያስቡ ምናልባትም ፊልም ላይ እንደሚያዩት ጺሙ የተንዥረገገ፣ፊቱ የተኮሳተረ፣ በቀኝ እጁ ቁርአን በግራ እጁ ሰይፍ የያዘ ሰዉ በአይነ ህሊናቸዉ ሊመጣባቸዉ ይችላል፡፡ ይህም ሰዉ ከፊት ለፊቱ ያገኘዉን ሁሉ “ትሰልማለህ ወይስ አትሰልምም” በማለት ይጠይቃል “ሰልሜያለዉ” ያለዉን ይተዋል “አልሰልምም” ያለዉን ግን “አሏሁ አክበር” በማለት አንገቱን በሰይፍ ይቀላል ወይም ደግሞ ቦንብ አንግቦ ሰላማዊ ህዝብ የተሰበሰበባቸዉን ቦታዎች በማጋየት ንፀሃንን ሲጨርስ ይታያቸዋል፡፡ https://hidayacomparative.org/?p=14 ወቅቱ በ1930 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠርር ነበር፤ የግብፁ አል-አዝሀር ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንግዳ ነገር ተሰማ። በሳሙኤል ዚውመር የተመራው የሚሽነሪ ቡድን ያለምንም ፍርሀት ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ዘልቆ በመግባት የተለያዩ ፓምፍሌቶችንና ብሮሹሮቹን በተነ።በተግባሩ የአዝሀር ዑለሞች ተቆጡ፤ “ፈጽሞ አይደረግም” በሚል ሀሳብ ያንቀላፉት ሳይቀር ባለማመን ሰመመን ውስጥ ሁነው ድንጋጤ አላወሳቸው። የሁሉም ጥያቄ ግን “እነዚህ አካላት በዚህ ደረጃ እንዴት ደፈሩ?” መካ በእስልምና ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው እና ቅዱስ ከሆኑ የአምልኮ ስፍራዎች ግንባር ቀደሟ ሀገር (ከተማ) ናት። ጌታ አምላካችን በክብር አልቆ የማለበት ሀገር (ሱራ 90:1) ከመሆኗም ባሻገር የነቢያቶች አባት የሆኑት አብረሃም ጸጥተኛ (የሰላም) ሀገር ትሆን ዘንድ በጸሎታቸው ያሰቧት ቅድስት ስፍራ ናት (ቁርኣን 2፥126)። በዚህች ጸጥተኛ ከተማ (መካ) ውስጥ ነቢዩ አብረሃም ከልጁ ኢስማኤል ጋር ለሰዎች የአምልኮ ቦታ ይሆን ዘንድ የቤተመቅደስን መሰረት ከፍ አድርገው እንዳቆሙ (እንደገነቡ) ቁርኣን እንዲህ በማለት ይናገራል:- https://hidayacomparative.org/?p=879 ብሪታንያዊው የታሪክ ጸሐፊና ሚሺነሪው ዊልያም ክሌር በ1905 በጻፈው “The Original Sources Of The Qur’an” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ነቢዩ ሙሐመድ ከቀደሙት መጽሐፍት ማለትም ከአይሁዳውያን ጹሑፍ፣ ከባይብል፣ ከዞርስትያንስ፣ ከሳቢያኖች እና ከጣዖታዊያን ኮርጀዋል በማለት የተለመደውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ከፍተው ከደሰኮሩ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ ሲሆን እርሱም እንደ ቀደሙት ተቺዎች ሞተው ከበሰበሱት ውስጥ ነው። ለነቢያችን የመጣው መገለጥ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ እንደሆነ ቁርዓን ይነግረናል ከሃዲዎች ከነቢያችን ዘመን ጀምረው ቁርዓንን ላለመቀበል ከሚያቀርቧቸው ማስተባበያዎች ውስጥ አንዱ ቁርዓን ከሌላ መጽሐፍ ዘንድ ኮርጇል የሚለውን ጸለምተኛ ክስ ነው:: ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ይህ ብሪታንያዊው ተቺ ከላይ በተመለከትነው መጽሐፉ ላይ “ቁርዓን የአዳምን ሁለት ልጆች (ሀቢል እና ቃቢልን) ታሪክና ንግግር ከአይሁዳውያን ጹሑፍ ማብራሪያ ማለትም ከ “ታርጉም ዮናታን” እና ከ “ታርጉም የሩሰሌም” (Pirqey Rabbi Eli’zer” እና “Mishnah Sanhedrin) የተኮረጀ ነው በማለት እንዲህ ብሎ ይጽፋል ‟conversation, or rather argument, between Cain and Abel is mentioned in Jewish legend both in the Targum of Jonathan 14 and in the Targum of Jerusalem” https://hidayacomparative.org/?p=877 ሚስዮናዊያን ቁርኣን ላይ ከሚከፍቷቸው ክሶች መካከል ‟ቁርኣን ከፊቱ ያለውን ታሪክ ከሌላ ጹሑፍ ገልብጧል (ኮርጇል)” የሚል ነው፣ ይህ ክስ ጥንትም በቁረይሾች ተነስቶ እንደነበር ይታወቃል፣ ዛሬም በምዕራቡ ዓለም ሰባኪዎች እና በአንዳንድ የሃገራችን ወገኖች በተደጋጋሚ ይነሳል። ተኮርጇል ተብሎ የሚቀርበውን ታሪክና የተኮረጀበት ቀዳሚው ምንጭ ይህ ነው ብለው ሲያቀርቡ ሁሌም ግርም ይለኛል። ለማንኛውም ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስንመጣ ገብርኤል ሳይድ ሪይኖልድስ የተባለው ጸሐፊ “The Qur’an in Its Historical Context” በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 175-80 ላይ ቁርኣን የዙልቀርነይንን ታሪክ ከሲሪያኩ ጹሑፍ ‟ኒሻነህ ዲሌህ አሌክሳንድሮስ” ወይም “የአሌክሳንደር ግሩም ስራዎች” በመባል ከሚታወቀው ጹሑፍ ነው የተቀዳው በማለት ይጽፋል። https://hidayacomparative.org/?p=872 የነቢዩን ሐያዕ እና ውብ ሥነ-ምግባር ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት እና ለማደብዘዝ ሌት-ከቀን የሚሰሩ አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት በርካታ የሕይወት ታሪካቸውንና ንግግራቸውን ከማጥመምም አልፈው ሐዲስ እስከ መፈብረክ እንደ ደረሱ ይታወቃል። ሐሰተኛ ነው የሚሉትን ነቢይ በእውነት ሚዛን ሐሰተኛ ማድረግ ስላልቻሉ መሰረት አልባ ክሶችን ማዘውተር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከእነርሱ መካከል ከታች የሚገኘውን ሐዲስ በማጥመም ነቢያችሁ የብልግና ቃል ተናግረዋል ይላሉ:- https://hidayacomparative.org/?p=869 […] የሚለውን ነጥብ እንመልከት:- https://hidayacomparative.org/?p=861